የሚታዩ መተግበሪያዎች
በመተግበሪያዎች እና መሳሪያዎች ከOneNote ውስጥ ተጨማሪ ነገሮችን ያግኙ።
Brother Web Connection
የእርስዎ ወንድም ማሽን (MFP/የሰነድ ስካነር) ምስሎችን ስካን ያደርጋል አንዲሁም ወደ OneNote እና OneDrive በኮምፒውተርዎ ውስጥ ሳያልፍ በቀጥታ ይሰቅላል።
Chegg
ተማሪዎች የወሳኝ የቤት ስራ ምላሻቸውን ከ Chegg Study Q&A ወደ OneNote ማስቀመጥ ይችላሉ። በ OneNote «ቁረጠው» አዝራርን በመጠቀም ይህንን ማድረግ ቀላል ነው። ከዚያ በመነሳት መልሶችዎን በትምህርት አይነት፣ በክፍል ወይም በቤት ሰራ ማደራጀትና ሁሉም በፍጥነት በ OneNote ውስጥ መፈለግ የሚችሉ ማድረግ ይችላሉ። ምርጡን የጥናት መመሪያ ይፍጠሩና ከክፍል ጓደኛዎችዎ ጋር ይጋሩት።
cloudHQ
ያንተን OneNote ማስታወሻዎች በcloudHQ አቀናጅ። ማስተወሻ ደብተሮችህን በሌሎች ታዋቂ የክላውድ አገልግሎቶች ለምሳሌ Salesforce፣ Evernote እና Dropbox ተጠቅመህ አመሳስል። ከሌሎች ጋር በቀላሉ ተባበር፣ ሀሳቦችህን ማንኛውም መተግበሪያ ላይ አጋራ እና መልሰህ OneNote ላይ አመሳስላቸው። እንዲሁም ሀሳቦህን በድንገት ሰርዘሃቸው እንዳይጠፉ ለማድረግ የ OneNote ማስታወሻ ደብተሮችህን ሌሎች የክላውድ አገልግሎቶች ላይ ተጠባባቂ አስቀምጥላቸው።
Newton
Newton በመጠቀም በአንድ ጠቅታ ብቻ አስፈላጊዎቹን ኢሜልዎች ወደ OneNote ያስቀምጡ። ደረሰኝ፣ የምግብ አሰራር፣ ወይም አስፈላጊ የደንበኛ ኢሜይል ይሁን፣ ሁሉንም ነገር አንድ ላይ ለማቆየት የ Newton OneNote ውህደት ይጠቀሙ።
Docs.com
Docs.com ተጠቃሚዎችን ማስታወሻዎች ወይም የማስተማሪያ መሳሪያዎች በ OneNote ማስታወሻ ደብተሮች እንዲያሰራጩ ይፈቅዳል። በማህበረሰቡ ታዋቂነት እና ተጽዕኖ በመፍጠር፣ በዓለም ሁሉ ያሉ አስተማሪዎች እና ተማሪዎች የማስታወሻ ደብተር እንዲመለከቱ እና እንደገና እንዲጠቀሙ ይፈቅዳል።
Doxie Mobile Scanners
Doxie በተደጋጋሚ ቻርጅ ሊደረግ የሚችል አዲስ አይነት ስካነር ነው፣ ስለዚህ ሰነዶችን በማንኛውም ስፍራ ላይ ሆነው ስካን ማድረግ ይችላሉ - ምንም ኮምፒውተር አያስፈልግም። በቃ ቻርጅ ያድርጉት እና ያብሩት፣ የትም ቦታ ቢሆኑ - ወረቀትዎን፣ ደረሰኞችን፣ እና ፎቶዎችን ስካን ለማድረግ፣ ለመመዝገብ እና ለማጋራት ያስገቡ። Doxie በማንኛውም ስፍራ ስካን ያደርጋል፣ ከዚያም ስካን የተደረጉ ሰነዶችን በሁሉም በእርስዎ መሳሪያዎች ላይ ለማግኘት ከOneNote ጋር ያሰባጥራል።
EDUonGo
EDUonGo ማንኛውም ሰው የመስመር ላይ አካዳሚ ወይም ኮርስ በደቂቃዎች ውስጥ መጀመር እንዲችል ያርጋል። የEDUonGo ተማሪዎች ትምህርቶችን ወደራሳቸው ማስታወሻ ደብተሮች በቀላሉ መላክ ይችላሉ። በዚህም ተማሪዎች በቀላሉ ማስታወሻዎችን መያዝ እና ለሌሎች ማጋራት ይችላሉ። ተማሪዎች ከዚህ በተጨማሪ ከራሳቸው የOneDrive መለያዎች ጋር መገናኘት ይችላሉ። እንደ መምህራን ከOffice Mix የተገኙ ቪዲዮዎችን ወደ ትምህርቶችህ ማካተት ትችላለህ።
ወደ OneNote ኢሜይል ያድርጉ
በሚሄዱበት ጊዜ እርስዎ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ይያዙ እና በቀጥታ ወደ እርስዎ ማስታወሻ ደብተር ይላኩ! ሰነዶን፣ ማስታወሻዎችን፣ የጉዞ መግለጫዎችን፣ እና በርካታ ነገሮችን ወደ me@onenote.com ይላኩ እና በእርስዎ OneNote ማስታወሻ ደብተር ውስጥ እናስቀምጠዋለን፣ ይህም እርስዎ ከሁሉም መሳሪያዎችዎ ላይ ሆነው መድረስ የሚችሉበት ነው።
Epson Document Capture Pro
Document Capture Pro ሰነዶችን በቀላሉ ስካን እንዲያደርጉ፣ ገፆችን አርትዕ እንዲያደርጉ፣ ፋይሎችን እንዲያስቀምጡ፣ እና እንደ Workforce® DS-30፣ DS-510፣ DS-560 እና ሌሎች የEpson ስካነሮች ስካን የተደረገ ውሂብን ወደ መተግበሪያዎች ለማስተላለፍ ያስችልዎታል። በተጨማሪም፣ ተጠቃሚዎች በአንድ ንኪ ብቻ ተጠቃሚዎች በOneNote ስካን ያደርጋሉ፣ ይህም በመልቲሚዲያ መሳሪያዎች ውስጥ ያሉ ሰነዶችን ላይ በቀላሉ ለመድረስ እና ከሌሎች ጋር ለመጋራት ያስችላቸዋል።
eQuil Smartpen2 & Smartmarker
በማንኛውም ገጽታ ላይ ማስታወሻዎችን ጻፍና OneNote በeQuil Smartpen2 እና Smartmarker የላቀ ገጽታ በማድረግ ወደ OneNote ላካቸው። ምርጥ ሀሳቦችዎ የሚያዙበት ተፈጥሯዊ መንድ ነው።
Feedly
Feedly አንባቢዎችን ከታሪኮች እና እነርሱ ከሚወዱዋቸው መረጃዎች ጋር አጥጋቢ በሆነ መልኩ ያገናኛል። በጣም ጥሩ ይዘቶችን ለማግኘት እና ለመከታተል Feedly ይጠቀሙ፣ ከዚያም በጣም ቆንጆ የሆነውን መጣጥፍ በቀጥታ አንድ ጊዜ ጠቅ በማድረግ በOneNote ላይ ያስቀምጡ።
Paper እና Pencil በ FiftyThree
ሃሳብዎን Pencil ወደ Paper ይውሰዱና ከዚያ በ OneNote አንድ ደረጃ ያራምዱት። በተሻሻለው፣ ጥራት ባለውና ቀላል በሆነው Pencil ይጻፉ እንዲሁም ይሳሉ እና ከተሳሳቱ ሰቲለሱን ይገልብጡና ተፈጥሮዋዊ በሆነ መንገድ በቀጥታ በ OneNote ውስጥ ያጥፉት። በቀላሉ ማስታወሻ ይያዙ፣ በ Paper ላይ የማረጋገጫ ቅጽ እና ንድፎችን ይስሩ ከዚያ ተጨማሪ ለመሰራት ለምሳሌ በተጋራ ማስታወሻ ደብተር ላይ ለመስራት፣ የኦዲዮ ቅጂዎችን ለማከልና ይዘተዎ ላይ በደፈናው ከማንኛውም መሳሪያ ላይ ለመድረስ ለ OneNote ያጋሩ።
Genius Scan
Genius Scan በእርስዎ ኪስ ውስጥ ያለ ስካነር ነው። የወረቀት ሰነዶችን አሃዛዊ ለማድረግ ፣ PDF ፋይሎችን ለመፍጠር እና በፍጥነት በ OneNote ውስጥ ለማከማቸት ያስችልዎታል።
JotNot Scanner
JotNot የእርስዎን iPhone ወደ ተንቀሳቃሽ በርካታ ገፅ ወዳለው ስካነር ይለውጣል። ሰነዶችን፣ ደረሰኞችን፣ ነጭ ቦርዶችን፣ የአድራሻ ካርዶችን፣ እና ማስታወሻዎችን ወደ ኤሌክትሮኒክ ቅርፀት ለመለወጥ እና ስካን ለማድረግ JotNot መጠቀም ይችላሉ። JotNot አሁን ከMicrosoft's OneNote አቀማመጥ ጋር ቀጥተኛ ውህደትን ይሰጣል፣ ስለዚህ የእርስዎን OneNote መለያ በመጠቀም በፍጥነት እና በቀላሉ ስካን የተደረጉ ሰነዶችዎን ምትኬ መያዝ እና ማደራጀት ይችላሉ።
Livescribe 3 Smartpen
በLivescribe 3 smartpen እና Livescribe+ app፣ በቀላሉ በወረቀት ላይ ይፃፉ እና ሁሉም ነገር በእርስዎ ሞባይል መሳሪያ ላይ በፍጥነት ሲታይ ይመልከቱት፣ ይህም የእርስዎን ማስታወሻዎች ለማጣበቅ፣ ለመፈለግ እና ወደ ፅሁፍ ለመለወጥ የሚያስችልዎ ነው። ሁሉንም ነገር ወደ OneNote መላክ ይችላሉ ስለዚህም የእርስዎ በእጅ ፅሁፍ የተፃፈ ማስታወሻ እና ንድፎች ከእርሰዎ በጣም አስፈላጊ ቀሪ መረጃ ጋር ይዋሃዳሉ።
Mod Notebooks
ሞድ የወረቀት ማስታወሻ ደብተር ሲሆን ከክላውድ ላይ ሆኖ የሚደረስበት ነው። በተለመደ እስክሪብቶ እና ወረቀት ማስታወሻዎች ይውሰዱ፣ ገጾችዎ በነፃ አሃዛዊ ይደረጉ። የተጠናቀቀው ማስታወሻ ደብተር እያንዳንዱ ገፅ ወደ OneNote ሊሰባጠር ይችላል እና ለሁልጊዜውም መቀመጥ ይችላል።
NeatConnect
NeatConnect የወረቀት ስብስቦችን ያለ ኮምፒውተር ወደ አሃዛዊ ሰነዶች አስተላልፎ በቀጥታ ወደ OneNote ይልካል። በቤትዎ ውስጥ ከማንኛውም ክፍል፣ ወይም ከቢሮዎ ውስጥ ከማንኛውም ስፍራ፣ NeatConnect's Wi-Fi ተኳኋኝ እና የሚነካ ማያ ገፅ በOneNote ስካን ማድረግን ፈጣን እና ቀላል ያደርገዋል ስለዚህ ሰዓት መቆጠብ ይችላሉ፣ እንዲሁም የድርጅቱን ምርታማነት በአጠቃላይ ወደ አዲስ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።.
News360
News360 ነፃ ግላዊ የሆነ የዜና መተግበሪያ ሲሆን እርስዎ ምን እንደሚወዱ የሚያውቅ ነው እና እርስዎ መጠቀምዎን በጨመሩ መጠን የበለጠ እየተሻሻለ የሚመጣ ነው። ከ100,000+ በላይ ከሚሆኑ ምንጮች፣ ሁልጊዜም ለመነበብ የሚስብ የሆነ ነገር አለ፣ እና የእርስዎ ተወዳጅ የሆኑ ታሪኮችን በቀጥታ አዝራርን በመንካት በOneNote ላይ ማስቀመጥ ይችላሉ።
Nextgen Reader
ፈጣን፣ ንፁህ እና ቆንጆ RSS አንባቢ ለWindows Phone። አሁን መጣጥፎችን በቀጥታ በOneNote ላይ ለማስቀመጥ ያስችልዎታል። መልካም ንባብ!
Office Lens
Office Lens በኪስዎ ውስጥ ስካነር እንዳለዎ አይነት ነገር ነው። በነጭ ሰሌዳ ወይም በጥቁር ሰሌዳ ላይ ያሉ ማስታወሻዎችን መቼም አያመልጥዎትም፣ እና በትክክለኛው ስፍራ ያልተቀመጡ ሰነዶችን ወይም የአድራሻ ካርዶችን፣ ደረሰኞችን እና የሚጣበቁ ማስታወሻዎችን ለማግኘት መቼም ቢሆን በድጋሚ ፍለጋን አያካሂዱም! Office Lens የእርስዎን ምስሎች ምትሃታዊ በሆነ መልኩ የሚነበቡ ወይም ዳግም ለአገልግሎት የሚውሉ ያደርጋቸዋል። ይዘቱን በቀጥታ በOneNote ውስጥ ከራስ ሰር መቁረጫ እና ማፅጃ ጋር ይያዙት።
OneNote For AutoCAD
OneNote ለ AutoCAD በ AutoCAD ውስጥ ከስእሎችዎ ጎን ለጎን ማስታወሻዎችን እንዲወስዱ ይፈቅድልዎታል። ይህ ደግሞ AutoCAD በመጠቀም 2D እና 3D ስእሎች ለመፍጠር በመላው ዓለም ያሉ የስነ-ህንጻ እና የምህንድስና ባለሙያዎች ምርታማነታቸውን ያሳድጋል። እነዚህ ማስታወሻዎች ወደ ደመናው በምትኬ ይቀመጣሉ እና በማንኛውም ጊዜ መዳረስ ይቻላል። ተጠቃሚዎች የሚቀጥለው ጊዜ ስእሉን በ AutoCAD በሚከፍቱበት እነዚህ ማስታወሻዎች ሊያዩ ይችላሉ።
OneNote Class Notebooks
ለእያንዳንዱ ተማሪ ከግላዊ የስራ ቦታ፣ ለሚታደሉ ጽሑፎች ቤተ ይዘት፣ እና ለትምህርቶች እና የፈጠራ እንቅስቃሴዎች የትብብር ቦታ ጋር የትምህርት ዕቅድዎ እና የኮርስ ይዘት በአሃዛዊ ማስታወሻ ደብተርዎ ያደራጁ።
OneNote Web Clipper
የOneNote የድር መቀንጠቢያ የድር ገፆችን ከእርስዎ ማሰሻ ላይ ወደ እርስዎ OneNote ማስታወሻደብተሮች ለማስቀመጥ ያስችልዎታል። አንድ ጊዜ ጠቅ በማድረግ፣ በህይወትዎ ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በፍጥነት ለመያዝ እና ለማስታወስ ያግዝዎታል።
Powerbot for Gmail
አስፈላጊ ኢሜይሎች፣ ንግግሮች እና አባሪዎችን በቀጥታ ከ Gmail ምልልስ ወደ OneNote ያስቀምጡ። በትግበራዎች መካከል ወዲያና ወዲህ መዝለል ከእንግዲህ የለም።
WordPress
WordPress ላይ ያወጣሃቸውን ነገሮች ማንኛውም መሳሪያ፣ የተለያየ ቦታ፣ መስመር ላይ ወይም ከመስመር ውጭ OneNote ላይ አደራጅ እና ካሉህ ሁሉም ማስታወሻች የተገኘ ይዘትን በቀላሉ መልሰህ ተጠቀምበት።
Zapier
እንደ Salesforce፣ Trello፣ Basecamp፣ Wufoo እና Twitter ያሉ ቀድሞውኑ ከሚጠቀሙዋቸው መተግበሪያዎች ጋር በአንድ ላይ በመሆን ከOneNote ጋር ለመገናኘት Zapier ቀላሉ መንገድ ነው። የማስታወሻዎችን ምትኬ ለማስቀመጥ፣ የተጠናቀቁ ተግባራትን ሰነድ ለማስቀመጥ፣ ወይም አዲስ እውቂያዎችን፣ ፎቶዎችን፣ የድር ገፆችን እና ተጨማሪ ነገሮችን ለማስቀመጥ ይህንን መተግበሪያ ይጠቀሙ።